ጳጉሜ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ሶስት የአማራ ከልል ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የተሰወሩ ሲሆን፣ በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ ሪፖርቶች እየቀረቡ ነው።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ስርዓቱን ከመንበሩ የሚያወርደው ሰራዊቱ እንደሆነና ይህም ብዙ ጊዜ እንደማይፈጅባቸው በአጽንኦት እየተናገሩ ነው፡፡በተለይ የደቡብ ክልል ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትበከፍተኛ ደረጃ በህውሃት አመራሮች መማረራቸውን በግልጽ የሚናገሩበት ወቅት መድረሳቸውን የፌደራል ፖሊስ አባላት ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ወደ ህዝብ ትግል ለመቀላቀልበውስጣቸው እየተዘጋጁ መሆኑን የሚናገሩት አባላቱ፣ ስርዓቱ ‹‹የተነቃነቀ ጥርስ ›› ሆኗል ብለው ያምናሉ፡፡ የወያኔ አመራሮች በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ላይ በመመሆናቸው በየጊዜው የሚያደርጉትንእያሳጣቸው መሆኑ፣ ሰራዊቱ በስርዓቱ ላይ እምነት እንዲያጣ እያደረገው
መሆኑን እነዚሁ የሰራዊቱ አባላት ይናገራሉ።