አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እየተጠበቀ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010)

በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል የአገዛዙ የደህንነት ሃይሎች ግቢውን በአይነቁራኛ እየተከታተሉ መሆናቸው ተነገረ።

በዩኒቨርስቲው ትላንት ተቃውሞ ለመጀመር ተማሪዎች ቀጠሮ ይዘው እንደነበር ይነገራል።

የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ተማሪዎች በጥርጣሬ ብቻ እየታፈኑ በፒካፕ ተሽከርካሪ ወደ ማጎሪያ ቦታ መወሰዳቸው ተነግሯል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲቪል የለበሱ በርካታ ፖሊሶች መግባታቸውንም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል።

የሕወሃት አገዛዝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ከተነሳ የአዲስ አበባ ሕዝብም ተመሳሳይ ርምጃ ሊወስድ ይችላል በሚል በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።