አዲሱ የጉምሩክ ረቂቅ አዋጅ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በፍርቤቶች ሊወሰን የሚገባ ጉዳዮችን እንዲወስን የተለ የመብት መስጠቱ አነጋጋሪሆነ፡፡

ሰኔ ፲፩(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሰሞኑን ለፓርላማው የቀረበ ሲሆን በዚሁ አዋጅ በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ብቻ ክስ የማይመሰረትባቸው ድንጋጌዎች ማካተቱ በፓርላማ አባላቱ ዘንድ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

ረቂቅአዋጁ “ለሕዝብጥቅምሲባል በዋና ዳይሬክተሩ ውሳኔ ክስ የማይመሰረትባቸው አዲስ ሁኔታዎች በሚል ከዘረዘራቸው ውስጥ ወንጀል ፈጽሞአል የተባለ ሰው በዕድሜ መጃጀት ወይም በበሽታ ምክንያት ጉዳዩን በፍርድ ቤት መከታተል የማይችል ሲሆን ፣ጉዳዩ በክስሒደትውስጥቢያልፍብሔራዊደህንነትንወይምዓለምአቀፍግንኙነትንይጎዳልተብሎሲታመን፣የክሱመመስረትተመጣጣኝናሚዛናዊያልሆነየጎንዮሽጉዳትየሚያስከትልመሆኑከታመነበት፣ወንጀሉስልጣንላለውፍርድቤትሳይቀርብበመቆየቱአስፈላጊነትያጣከሆነ ክስ እንዳይመሰረትዋና ዳይሬክተሩ ሊወስን እንደሚችል ደንግጎጓል፡፡

እነዚህ ድንጋጌዎች የፍርድ ቤቶች ሰልጣን እንጂ የአንድ መ/ቤት ሃላፊ ወይም ዋና ዳይሬክተር ስልጣን እንደማይሆን በመጥቀስ ድንጋጌዎቹ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ቀዳዳ የሚከፍቱ ጭምር በመሆናቸው እንዲሻሻሉ አንዳንድ ፓርላማ አባላት ጠይቀዋል፡፡

በተለይየአንድሰውየዕድሜመጃጀትምሆነጉዳዩንበፍርድቤትቀርቦመከታተልአለመቻል የሕክምናማስረጃጭምርየሚፈልግጉዳይመሆኑንበመጥቀስይህጉዳይበዋናዳይሬክተሩውሳኔእንዲሰጥበትየተፈለገበትምክንያትግልጽአለመሆኑአስተያየትተሰጥቶበታል፡፡

ይህአዲስአዋጅጥፋቶችተፈጽመውበሚገኙበትጊዜአጥፊውንሁሉበቁጥጥርስርበማዋልጉዳዩለፍርድቤትቀርቦውሳኔእስኪያገኝሰዎችለእንግልትናእስርየሚዳረጉበትሁኔታንለማስቀረትአዋጁንበመተላለፍየሚፈጸሙጥፋቶችእንደክብደታቸውመጠንበአስተዳደራዊእናበእስርናበገንዘብቅጣትየሚታይበትሁኔታማካተቱእንደበጎጎንታይቶአል፡፡አዋጁለሚመለከተውቋሚኮምቴተመራሲሆንከሰኔ 30 በፊትይጸድቃልተብሎይገመታል፡፡