ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ639 ሚሊዮን ዶላር በጀት አጽድቋል። ይህም አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አራት አገራት እንደሚውል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (USAID) አስታውቋል።
ከአራቱ አገራት አገራት ውስጥ በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያ አልተካተተችም። ናይጀሪያ121 ሚሊዮን፣ ደቡብ ሱዳን 199፣ ሶማሊያ 126 ሚሊዮን እና የመን 191 ሚሊዮን ዶላር እያንዳንዳቸው እንደሚያገኙ ዩ ኤስ ኤ ኣይ ዲን ጠቅሶ ዴይሊ ትረስት ዘግቧል።