አዲሱ የኢትዮጵያ መሪ የሰብአዊ መብቶች እንዲሻሻሉ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ሂውማን ራይትስ ወች አሳሳበ

ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ አዲሱ መንግስት መሰረታዊ የሚባሉ መብቶችን እንዲያከብር ፣ ቀደም ብለው የወጡ ህጎች እንዲሰረዙ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጠዋል።

የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ወኪል የሆኑት ሌስሊ ሌፍኮው “አዲሱ መንግስት መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር፣ አቶ መለስ የሰሩዋቸውን መልካም ስራዎች በመጠበቅ፣ በእርሳቸው ጊዜ የወጡ አደገኛ ህጎችን በመቀልበስ ለኢትዮጵያውያን መተማመኛና ተስፋ መስጠት አለበት” ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘን እንደተሰማቸው፣ ለኢትዮጵያ እድገት ያደረጉትን አስተዋጽኦ፣ ለአፍሪካ ሰላም መከበር የሰሩትን ስራ አወድሰዋል። የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ የልማት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ጎዳና ትገባ ዘንድ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጠዋል።

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide