ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ድርጅት ትናንት ባወጣው ጽሁፍ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት ሽመልስ ከማል በኢንተርኔት የሚደረጉ የኢንተርኔት የስልክ ልውውጦችን አናግድም በማለት ቢናገሩም ተቀባይነቱ አጠራጣሪ ነው ብሎአል።
ድርጅቱ እንደሚለው፣ የጸረ ሽብር ህጉ አሻሚ የሆኑ አንቀጾችን በመያዙ ጋዜጠኞችን ለማጥቂያነት መዋሉን በአስረጅነት የጠቀሰው ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ ፣ አዲሱ የቴሌኮሙኒኬሽን አዋጅም ጋዜጠኞችን እና ሌሎች ወገኖችን ሁሉ ለማጥቃት ሊውል ይችላል በማለት ስጋቱን ገልጧል።
ስካይፒና ሌሎች ዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች እንደማይታፈኑ አቶ ሽመልስ ቢናገሩም አቶ በረከት ስምኦን ግን ከኢኮኖሚና ከደህንነት አንጻር ስካይፒና ሌሎች የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ይታገዳሉ ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide