አዲሱን ዓመት በደስታ ለመቀበል የሚጣደፍ ህብረተሰብ አለመኖሩ ገዥውን መንግስት አሳስቦታል፡፡

ጳጉ (አራት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ የዘመን መለወጫ ቀንን ለመቀበል ከአሁን በፊት ሲታይ የነበረው ጥድፊያና ጉጉት ባለመታየቱ ከተማዋን ለሟሟቅ በተለያዩ

ሱቆችበራፍና መንገድ ላይ በርካታ የድምጽ

ማጉያዎችንበመከራየት ልዩ ልዩ ዘፈኞችን በመክፈት ለሟሟሟቅ የሚደረገው ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል፡፡

ነዋሪዎች እንደሚናገሩት  ከአሁን በፊት የነበሩት በዓላት በአዲስ ተስፋ ሲቀበሉ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን ህዝቡ ተገዳይ በሆነበት ጊዜ ላይ ቆመው እንዲህ አይነቱን የበዓል ግርግር ለመቀበል

ህሊናቸውአይፈቅድም፡፡

በአዲስ አበባ በመላው ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች  በጥቃቅንና አነስተኛ የሚንቀሳቀሱ ኢንተርፕራይዞች የመንገድ ላይ ባዛር

እንዲያካሂዱ ግፊት ተደርጎባቸው ቢያካሂዱም የሸማቹ ቁጥር መቀነሱእንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር  ለአዲሱ አመት የተዘጋጀውን ሎተሪ ከአሁን በፊት እንደነበረው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ህብረተሰቡ ተሻምቶ አለመግዛቱ

እንዳስደመማቸው ሎተሪ አዟሪዎች ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ የህብረተሰቡ ክፍሎች ‹‹ ሎቶሪ በመግዛት ወገኖቻችን የሚያልቁበትን ጥይት መግዢያ ለህውሃት መንግስት አናቀብልም ›› በማለት ለመግዛት

ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

የሎቶሪው እጣ መውጪያ አንድ ቀን ቢቀረውም በርካታ የሎቶሪ ትኬቶች በእጃቸው ላይ እንዳለ አዟሪዎች ገልጸዋል፡፡