ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የአለማቀፍ የስደተኞች ኮምሽነር ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን በሜዲትራኒያን ባህር በሰጠመችው ጀልባ ከነበሩ ከ800 በላይ የተለያዩ አገር ዜጎች መካከል 350 ኤርትራውያን ናቸው ተብሎ
እንደሚገመት ገልጾ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ጋምቢያ፣ አይቮሪኮስት እና ባንግላዲሽ የመጡ መሆናቸውን ዘግቧል።
አይ ኦ ኤም የተባለው አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት ደግሞ በዚህ አመት ከ30 ሺ በላይ የውጭ አገር ዜጎች በሜድትራኒያን ባህር ላይ ሊሞቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ከ 1 ሺ 700 በላይ ዜጎች ባህሩ ላይ ማለቃቸውን የገለጸው አይ ኦ ኤም፣
በአመቱ መጨረሻ ከ30 ሺ በላይ ስደተኞች ሊያልቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።