ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ወደ ተክለሀይማኖትና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚወሰድው መንገድ ላይ በርካታ ህጻናት ጎዳና ላይ ውለው ያድራሉ። ትናንት ከጧቱ 4 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ነው። አንድ አዲስ አበባ ፖሊስ አባል አንድ በልመና የሚተዳደርን የጎዳና ተዳዳሪ ይደበድበዋል። የጎዳና ተዳዳሪውም በድብደባው ህይወቱ ያልፋል። ድብደባውን የፈጸመው ፖሊስና ጓደኞቹ በፍጥነት ከአካባቢው ይሰወራሉ። ትንሽ ቆይቶም ሌሎች ፖሊሶች በብዛት መጥተው አካባቢውን በመቆጣጠር ሟቹን ለመውሰድ ይሞክራሉ። የአካባቢው ሰዎች ግን ማቹን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከፖሊሶች ጋር ተጋጭተዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአዲስ አበባ ከጨረቃ ቤቶች መፍረስ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን ዘጋቢያችን ገልጧል። በተለምዶ የጨረቃ ቤቶች እየተባሉ የሚጠሩ በተለይም የገዢው ፓርቲ ሰዎች በምርጫ 97 መሸነፋቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባን መሬት እንደልባቸው በመቸብቸብ በርካታ ቤቶች እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ካመቻቹ በሁዋላ፣ ሰሞኑን ቤቶቹ እንዲፈርሱ የሚል ትእዛዝ መተላለፉ የውጥረቱ መነሻ ሆኗል።
የፌደራል እና የመስተዳዳሩ ፖሊሶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ፣ ቤት የማፍረሱን ሂደት ተከትሎ ለሚነሳ ውዝግብ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል።
በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጨረቃ ቤቶች ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል።___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide