አንድ ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ ተደብቆ ስዊድን ገባ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነቱ ያልተገለጠው ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስት በመሆን ከ10 ሰአት ከ25 ደቂቃ በረራ በሁዋላ አርላንዳ አየር ማረፊያ ደርሷል። ግለሰቡ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ስደተኝነት መጠየቁም ታውቋል።

ነሃሴ ወር ውስጥ አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስጥ ሆኖ ስዊድን መግባቱ ይታወቃል። በሌላ ዜና ደግሞ በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተገድሏል።
ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች ከአካባቢው መሰወራቸውን የፖሊስ አዛዡ ሌተናል ኮሎኔል ሎንጌሎ ድላማኒ አስረድተዋል።
በተጨማሪም ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ ኬንያ ውስጥ ድንበር ላይ በፓሊስ የተያዙት 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በክዌኬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ሕገወጥ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ባለፈው ሳምንት በክዌክዌ በሚገኘው የአገሪቱ የአየር ኃይል ማሰልጠኛ ተቋም አቅራቢያ ተደብቀው ተኝተው እንዳሉ በፓትሮል መኪና አሰሳ ሲያደርጉ የነበሩ ሶስት ቃኚ ወታደሮች፣ ስደተኞቹን ተደብቀው ከተኙበት ጫካ ውስጥ መያዛቸውን ፓሊስ ጠቅሷል። ሙሉመን መንቶሴ ኬልቦሬ በተሰባባበረ እንግሊዝኛ የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ እያሉ መያዛቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናጋሯል።
ስደተኞቹ የኬንያ ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ማኅተም ያረፈበት ሕጋዊ ፓስፖርት መያዛቸውን ፍርድ ቤቱ ጠቅሷል። በቂ የሆነ አስተርጓሚ በማቅረብ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ብያኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለመጪው ረቡዕ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ኒውስ ዴይ ዘግቧል።