ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
የቅድመ ውህደት ስምምነት ፊርማ ካኖሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ውህደቱን ምሉዕ ለማድረግ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አስታውሰው፣ ለውህደቱ መሳካት
የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ሰፊ በመሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ደጋፊዎቻችን የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ በስምምነት ሰነዱ የተቀመጠው የውህደት ግዜ ላይ ሁለት ሳምንት
መጨመር እንደሚያስፈልግ በማመኑ ቀኑ መራዘሙን ገልጿል።
የሁለቱ ፓርቲዎች የውህደት ግዜ ሓምሌ 19 እና 20 እንዲሆን ስምምነት ላይ መደረሱን የገለጹት ፓርቲዎቹ፣የሁለቱ ፓርቲዎች ረቂቅ ደምብና ፕሮግራም ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁንም አውስተዋል።