አንድም ሰራዊት ለመንግስት እጅ አልሰጠም ሲሉ የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ አስታወቁ

ሐምሌ  ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ 400 የሚሆኑ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ወታደሮችና አመራሮች በድርድር እጃቸውን ሰጡ በማለት በመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው ዘገባ ሃሰት መሆኑን የድርጅቱ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ተናግረዋል።

ዶ/ር ኮንቴ እንዳሉት ከአመት በፊት የድርጀቱ ሊ/መንበር የነበረው አቶ አሎ አልዳየስ ከኮሎኔል ሙሃመድ አህመድ ጋር በመሆን ድርድር መጀመራቸው እንደታወቀ  በመጋቢት 2007 ዓም  ከሃላፊነት የተነሱ በመሆኑ፣ አሁን እንደ አዲስ  ዜናው መቅረቡ አስገርሟቸዋል። አቶ አሎ ከከናዳ ወደ ኢትዮጵያ ገቡ እንጅ የድርጅቱን ወታደሮች መርተው አልገቡም ሲሉ አክለዋል ። የአፋር ህዝብ ፓርቲ በጠንካራ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዶ/ር ኮንቴ በቅርቡም ከዚህ በፊት ከነበረው ለዬት ባለ ሁኔታ እንደሚፋፋም ገልጸዋል።