አንዋር መስጊድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ድርቅ ተመታ

ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ላለፉት 7 ወራት ከ50 ሺ ህዝብ በላይ ሲያስተናግድ የከረመው አንዋር መስኪድ በዛሬው የጁመአ ጸሎት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ100ዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ብቻ አስተናግዷል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ወደ አንዋር መስጊድ እንዳይሰባሰብ ተተኪ አመራሩ ውስጥ ለውስጥ ባሰራጨው መመሪያ መሰረት ፣ ህዝቡ ወደ መስጊዱ የሚያደርገውን ጉዞ እንደገታ ታውቋል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተል አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ሰው ለኢሳት እንደተናገረው ሙስሊሞ ዛሬ በአንዋር መስጊድ ያልተሰባሰበው፣ መንግስት ረብሻ ለማስነሳት ማቀዱ ስለተደረሰበት ነው::

1ሺ 433ኛው የኢድ አልፈጥር በአል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ነሀሴ 12 ዛሬ ፣ምሽት ጨረቃ ካልታየች ደግሞ ነሀሴ 13 እንደሚሆን ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በደሴ ከተማ የእስልምና እምነት አባቶች መደብደባቸውን፣ ሴቶች ማጽሀናቸው እየተረገጠ መገረፋቸውን እንዲሁም የደህንነት ሀይሎች የሙስሊሞችን ሞባይል እየቀሙ፣ አንዳንዶች ገንዘብ ካልሰጣችሁን አሸባሪ ብለን እንጠቁምባችሁዋለን በማለት ዝርፊያ እየፈጸሙ መሆኑን ግፉ የደረሰባቸው ሴቶች ለኢሳት ተናግረዋል።

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide