ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2008)
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በጀርመን ሃገር ተቃውሞ ገጠማቸው። በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት ከተማ ሰኞ ሰኔ 6 ፥ 2008 ከኢትዮያውያን ተቃውሞ የገጠማቸው አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቀመጫቸውን ለቀው ሲሄዱ ታይተዋል።
በተንቀሳቃሽ ምስል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ጌታቸው ረዳ ለደቂቃዎች ተቃውሞዎችን ያስተናገዱ ሲሆን፣ እርሳቸውም ተቃውሞ ያሰሙትን ሰዎች ለማግባባት ሲሞክሩ ታይተዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳን ያረፉበት ሆቴል ድረስ ተከታትለው ተቃውሞ ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን ለኢሳት እንደተናገሩት፣ አቶ ጌታቸው ድንገት ከሆቴሉ ወጥተው በመኪና ሸሽተዋል።