አቶ ጌቱ ገለቴና አቶ ገምሹ በየነ ወደ አገር ቤት ተመለሱ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 28/2010)በሙስና ተወንጅለው የነበሩትና ክሳቸው የተቋረጠላቸው የጌት አስ ኢንተርናሽናል ባለቤት አቶ ጌቱ ገለቴና የኢሊሊ ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ወደ አገር ቤት ተመለሱ፡፡

ሁለቱ ባለሃብቶች በሙስና ከተወነጀሉ በኋላ እንዳይታሰሩ በመፍራት በአሜሪካና በዱባይ ለአመታት ስደት ላይ ቆይተዋል።

በሙስና ክስ ተወንጀለው በርካታ ከፍተኛ ባለሃብቶች በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ሰሞኑን ክሳቸው ተቋርጦ በምሕረት መፈታታቸው ይታወሳል።