አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኛ ክስ ተመሰረተበት

ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016)

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ የጻፋቸው ጹሁፎችና አስተያየቶች በማስረጃነት ቀርበውበት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

ተከሳሹ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም አመጽና ብጥብጥን የሚያነሳሱ ጽሁፎች አሰራጭቷል እንዲሁም መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎች ጽፏል ተብሎ በከሳሽ አቃቢ ህግ ራሱ እንደተመሰረተበት ታውቋል።