አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበትን 2ኛ አመት ለማስታወስ ትዕይንት ተካሄደ

ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008)

የግንቦት 7 መስራችና ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡበትን 2ኛ ዓመት ለማስታወስ በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ትዕይት ተካሄደ። የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች በተገኙበት ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ ብሪታኒያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተካሄደው ህዝባዊ ትዕይንት የብሪታኒያ መንግስት ሃላፊነቱን በአግባቡ አልተውጣም የሚል ተቃውሞ ቀርቧል።

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታናሽ እህት እስከዳር ጽጌ እንዲሁም የእህታቸው ልጅ ህጻኗ ጀስቲስ ጽጌ የህዝባዊ ትዕይንት ታዳሚዎች እንደነበሩም መረዳት ተችሏል።

የግንቦት 7 ጸሃፊና መስራች የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ የታገቱት የዛሬ 2 ዓመት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ በትንሹ ለአንድ አመት ባልታወቀ ቦታ በስውር ታስረው መቆየታቸው ይታወቃል።

ከቅርብ ወራት ወዲህ ወደ ፌዴራል ወህኒ ቤት ቃሊቲ የተዛወሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው እንዲጎበኙ ቢደረግም የህግ ባለሙያ እንዲያገኙ አልተፈቀደም።

በኒውዮርክ እንዲሁም በሎሳንጀለስ የሚገኙት ዶ/ር ተቀዳ አለሙን በሌላ ለመተካት ስለመታሰቡ የታወቀ ነገር የለም።

የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ሰዎች የጸጥታ ጉዳይ በሚነሳባቸው እንዲሁም በትላለቅ ሃገሮች ላይ ቁጥራቸው እንዲጨምት የተፈለገበት ምክንያት በግልጽ አልተቀመጠም።