ኢሳት (ሃምሌ 4 ፥ 2008)
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ የቀረበባቸዉን የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ለመከላከል ምስክር ሆነዉ እንዲቀርቡላቸዉ ጥያቄ ላቀረቡ አምስት የፓርቲ አመራሮች በመከላከያ ምስክርነት ፍ/ቤት እንዲቀርቡ አዘዘ።
ሰበር ችሎቱ የመጨረሻ ዉሳኔውን ሰሞኑን ከማስተላለፉ በፊት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወራት በፊት አቶ አንዳርጋቸዉ ለተከሳሾቹ መከላከያ ምስክር ሆነዉ መቅረብ አይችሉም ሲል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል። ይሁንና ተከሳሾቹ በታችኛዉ ፍርድ ቤት በተላለፈዉ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ በመጠየቃቸዉ ምክንያት ሰበር ችሎት ዉሳኔውን በመቀልበስ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ለተከሳሾቹ መከላከያ ምስክር ሆነዉ እንዲቀርቡ ብይን መስጠቱ ታውቋል።
በተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረትም አቶ አንዳርጋቸዉ የፊታችን ሀሙስ ፍርድ ቤት በመቅረብ የምስክርነት ቃላቸዉን እንዲሰጡ ልዩ ትዕዛዝ ለቃሊቲ ፍርድ ቤት መሰጠቱን ከሀገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።
በእነ ዘመኔ ካሴ መዝገብ የተከሰሱ አምስት ተከሳሶች የቀረበባቸዉን የሽብርተኛ ወንጀል ለመከላከል ሲሉ አቶ አንዳርጋቸዉ ምስክር ሆነዉ እንዲቀርቡላቸዉ በተደጋጋሚ ጥያቄን አቅርበዉ የነበረ ሲሆን ከሳሽ አቃቢ ህግ ተከሳሾቹ ከአቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌ ጋር በአካል ተገናኝተዋል ሲል በክስ ቻርጁ ላይ አመልክቷል።
ይሁንና አምስቱ የፓርቲ አባላት አቃቢ ህግ ያቀረበባቸዉ ክስ ከእዉነት የራቀ ነዉ በማለት አቶ አንዳርጋቸዉ በአካል ቀርበዉ ጉዳዩን ለችሎት እንዲያስረዱ ጥያቄን አቅርበው ይገኛል።
ከቀናት በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለዉ የሚጠበቁት አቶ አንዳርጋቸዉ ከተከሳሾች ጋር በኤርትራ ምድር ስለመግናኘታቸዉ ቃላቸዉን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ተከሳሾች በበኩላቸዉ ፍርድ ቤት ተደጋጋሚ የሆነ ቀጠሮን በመስጠት ለእንግልት እየዳረገን ነዉ ሲሉ ቅሬታ ሲያቀርቡ