ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስተር መለሰ ዜናዊ ማለፋቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፖለትካ መድረከ ውስጥ ሚናቸው ጎልቶ የነበረው አቶ በረከት ስምአን ተጽእኖቸው አየቀነሰ የህዋሃት ጡንቻ አየፈረጠመ መምጣቱ ተገለጸ::
የአረና ትግራይ አመራር አባል የሆኑት አቶ አስራት አብርሃም የውስጥ ምንጮችን ጠቅሰው ባሰራጩት ጹሁፍ አንዳመለከቱት አቶ በረከት ስለ ኤርትራ የስጡት መግለጫ ህዋሃትን አሰተባብሮባቸዋል::
አቶ በረከት ስምኦን የኤርትራ ተቃዋሚዎች ፖልቶክ መድረክ ላይ ባድሜ የኤርትራ ነው በማለት መናገራቸው እና ኤርትራዊያን ከሃገር አንዲባረሩ ያደረጉት አቶ ስየ አብርሃም ናቸው ሲሉ መደመጣቸው የህዋሃት ሰዎች በአቶ በረከት ላይ አንዲነሱ ምክናየት መሆኑም ተመልክቷል::
አቶ በረከት ኤርትራዊያን ከሃገር አንዳይባረሩ እርሳቸውና አቶ መለስ መሞከራቸውን ሆኖም አቶ ተወልደ ወ/ማረያም : አቶ ስየአብርሃና አቶ ገብሩ አስራት የማባረሩ ሂደት ዋነኞቹ ተዋናዮች መሆናቸውን መስክረዋል::
አቶ በረከት በዚህ ረገድ የሰጡት መግለጫ የህዋሃትን ሰዎች በማስቆጣቱ ሚናቸው እየተገደበ ፡ተጽኑዋቸው እየቀነሰ መምጣቱን በዚህም የአቶ ሰብሃት ነጋ ቡድን እንዲያንሰራራ እድል መፍጠሩን ከጹሁፉ መረዳት ተችሏል::