የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ እንገለፀው፤ይህ የሆነው የክልሉ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ-ደኢህዴግ ከየካቲት 5 እስከ የካቲት 11 ቀን 2004 ዓመተምህረት ድረስ ባካሄደው ግምገማ ላይ ነው።
ቀደም ሲል በጋምቤላ በተደረገ ተመሣሳይ ግምገማ በ አኝዋኮች ጭፍጨፋ ተጠያቂ እንዲሆኑ ውሳኔ የተላለፈባቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦባንግ ኦሞድ፦” በ አኝዋኮች ግድያ እኔ የምጠየቅ ከሆነ፤ ድርጊቱ እንዲፈፀም ትዕዛዝ ያስተላለፈልኝ መለስ ዜናዊም መጠየቅ አለበት”ማለታቸው ይታወሳል።
ሰሞኑን በደቡብ በተካሄደው ግምገማ፤ የሲዳማ ቡና ላኪዎች ማህበር አባልና የማህበሩ ከፍተኛ ባለአክሲዮን እንደሆኑ በግምገማ የተረጋገጠባቸው ፕሬዚዳንቱ፣ ይህንኑ አስታከው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ጠንካራ አውጫጪኝ ተካሄዶባቸዋል።
እንደ አኢጋን መግለጫ ፤በኢህአዴግ የፖለቲካ ቋንቋ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፦ በ”ኪራይ ሰብሳቢነትና በሙሰኝነት” ተፈርጀዋል።
ይሁንና፤ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ወርደው በህግ እንዲጠየቁ ድርጅታዊ ውሳኔ ሲበየንባቸው፦ ”እኔ ብቻዬን አይደለሁም፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ከወይዘሮ አዜብ መስፍን ጋር በጋራ ነው ገንዘቡን የወሰድነው፡፡ የምንጠየቅም ከሆነ ሁለታችንም በህግ ፊት መቅረብ አለብን፡፡ ብሩን መመለስም ካለብን ፤ሁለታችንም እንመልስ” በማለት የግምገማ መድረኩን ረግጠው ወጥተዋል።
ይህ ሁኔታ ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረባቸው አቶ መለስ ዜናዊ በድርጅቱ የተላለፈውን ውሳኔ ሳያጸድቁ ቀልብሰውታል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የክልሉ አመራር፦ “የፓርቲው ውሳኔ የተገለበጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት በጉዳዩ ስላሉበት ነው። ውሳኔው በፓርቲው ውስጥ አለመተማመን ፈጥሯል” ይላሉ። እኚሁ የክልሉ አመራር አያይዘውም፦ “ፕሬዚዳንቱን በግልጽ ገምግመው ውሳኔ የወሰኑ ክፍሎች፤ እንዴት በቀጣይ አብረው ሊሰሩ ይችላሉ” ሲሉ ጠይቀዋል።
የጋምቤላው ፕሬዚዳንት በህግ እንዲጠየቁ የተላለፈው ውሳኔ በተመሣሳይ መንገድ በአቶ መለስ ትዕዛዝ እንደተቀለበዘ መዘገቡ አይዘነጋም።
የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሁለት ዓመት በፊት የሚቀናቀኗቸውን ሰዎች፦”የግድያ ሙከራ አድርገውብኛል”በማለት ማሣሰራቸው ሰፊ ተቃውሞ አስነስቶባቸው የቆየ ሲሆን፤ የታሰሩት ሰዎች በቂ መረጃ ሊቀብርብባቸው አልቻለም ተብለው ከእስር ነፃ ወጡት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው።
ብዙዎች፦”አቶ ሽፈራው ሽጉጤንና- ኢህአዴግን ያስተሣሰራቸው ገመድ እየተበጠሰ ይሆን?” በማለት መጠየቅ የጀመሩት፤ የአቶ ሽፈራው ተቀናቃኞች ከእስር የመፈታታቸው ዜና ሢሰማ ነበር።
አቶ ሽፈራው ድርጊቱን የፈፀምኩት ከወይዘሮ አዜብ ጋር ነው ማለታቸውና በህግ እንዲጠየቁ የተላለፈባቸው ውሳኔ በአቶ መለስ ተቀልብሷል መባሉ፤አቶ መለስ ከቡና ላኪዎች ገጋር ባደረጉት ስብሰባ ከመጋዘን ስለጠፋው 10 ሺህ ቶን ቡና የተናገሩትን እንድናስታውስ የሚያደርገን ነው ብለዋል አንድ የጋራ ንቅናቄውን መግለጫ ያነበቡ ኢትዮጵያዊ ::
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide