አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠው

መስከረም ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ከነሀሴ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የነበረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለሁለተኛ ጊዜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶታል።

ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዞ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍቤት ቀርቦ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም ተጨማሪ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ በመቀበል ለጥቅምት12 ቀን 2009 ዓ.ም. ድጋሜ እንዲቀርብ ሲል ብይን ሰጥቷል።