አብዬ የሚገኙት የሱዳን ወታደሮች ተመድ በዶላር ካልፈላቸው የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ።

ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-250 የሚሆኑት የሱዳን የተመድ የሰላም አስከባሪ አባላት፣ በአገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ህይወታቸውን ለመምራት ስላላስቻላቸው ፣ ተመድ በአገሪቱ ገንዘብ ከሚከፍላቸው በቀጥታ በዶላር እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። በሱዳን የሰፈሩት የተመድ የሰራዊት አባላት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ወርሃዊ ክፍያቸውን የሚያገኙት በብር ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቅሬታ ሲያቀርቡ አይሰማም። ከ10 አመት በፊት ድርጅቱ የሚከፍለን ገንዘብ በቀጥታ ይሰጠን በሚል ፍቼ ላይ ተቃውሞ ያነሱ ተመላሽ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ወደ ውቅሬ ተወስደው ከታሰሩ በሁዋላ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። የሱዳን ወታደሮች ላቀረቡት ጥያቄ ተመድ እስካሁን የሰጠው መልስ የለም።