አባት አርበኞች የፋሽስት ጣሊያን ዳግም ወረራ በተባበረ ክንዳቸው ያሸነፉበት 75ኛ ዓመት የድል በዓል በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ ውሏል።

ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋሽስት ጣልያን ጥሏት የነበረችው አርንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ቀለማት ያላት ስንደቅ አላማችን፤ በአርበኞች ደም ታጥባ ዳግም በሰንደቁ ጫፍ ላይ ከፍ ብላ ከተውብለበለች ዛሬ 75ኛ ዓመት ሆኗታል። የድል በዓል 75ኛው አመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በልዩ ሁኔታ መከበር ሲኖርበት ከወትሮው በተለየ መልኩ አለመዘከሩ አግባብ አለመሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተችተዋል። እለቱን በማስመልከት የጥንታዊነት ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በሰጡት አስየያዬት ፥ የአሁኑ ትውልድ አንገት አስደፊውን ድህነት ታግሎ በመጣል የአባቶቹን ጀግንነት ሊደግመው ይገባል ብለዋል።