ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ( አርዱፍ) 2ቱን ጀርመኖች የጠለፍኳቸው እኔ ነኝ አለ። ግለሰቦቹ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙም ገልጧል።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን በመጥቀስ ረዩተርስ እንደዘገበው፤ ቱርስቶቹ የተገዱለት በኢትዮጵያ ወታደሮች ነው በማለት ግንባሩ ለሟቾቹ የ ኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ አድርጓል።
በአካባቢው የአርዱፍ ግብረሀይል ቅኝት በማድረግ ላይ ሳለም፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እንደተከፈተበት -ግንባሩ ገልጧል።
በተኩሱ ልውውጥ መሀል 4ቱ የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገድለዋል ብሎአል-አርዱፍ።
አክሎም ከግንባሩ ጋር በእለቱ በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ 16 የኢትዮጵያ ወታደሮችም ተገድለዋል ብሎአል።
በቁጥጥሩ ስር ያሉት ጀርመናውያን እና ኢትዮጵያውያን በጥሩ ሁኔታ የሚገኙ መሆኑን የገለጠው አርዱፍ ፣ ሰዎችን በሽምግልና ለማስለቀቅ ሙከራ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል።
ግንባሩ ኤርትሪያ በጠለፋውም ሆነ በግድያው፤ እጇ የለበትም ሲልም የ ኢትዮጵያን መንግስት ክስ አጣጥሏል ።
አርዱፍ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በጂቡቲ የሚገኙ አፋሮችን አንድነት ለመመስረት የሚታገል ድርጅት ነው።