ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው በተለያዩ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በተካሄዱ የአገርን አድን ጥሪዎች ህዝቡ ለንቅናቄው ያለውን ድጋፍ ገልጿል። ብጹ አቡነ መቃርዮስና አቶ ብዙነህ ጽጌ በእንግድነት በተገኙበት በስዊዘርላንድ በተካሄደው ስብሰባ፣ ሴቶች በውድ ገንዘብ የተገዙ የእጅ አምባራቸውን ሰይቀር ለግሰዋል። በዝግጅቱም ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቧል።
የቶሮንቶ፣ ካልጋሪና ኦክላንድ ስብሰባዎችም እንዲሁ በጥሩ ውጤት መጠናቀቃቸው ተገልጿል።በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ጽጌ፣ ዶ/ር/ ሙሉአለም አዳምና የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ሊ/መንበር አቶ ዮሃንስ አለሙ በእንግድነት በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን ሊደግፉ ስለሚችሉበት ሁኔታ ተወያይተዋል።