አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ መብት አፈና አወገዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አሪድ ላንድስ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በ53ኛው የአፍሪካ የሰዎች እና የህዝቦች መብት ጉባኤ ላይ ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና በዝርዝር አቅርቧል።

አለማቀፍ ተሸላሚውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን፣ የኢንተርኔት ስርጭት እንዳይስፋፋ መደረጉን፣ መንግስት ከህዝቡ የሚሰበስበውን ገንዘብ የተለያዩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማፈኛነት እንደሚያውለው፣ ሽብርተኝነት በመዋጋት ስም የሚወጡት ህጎች ፕሬሱን እና ሌሎች መንግስታዊ ድርጀቶችን ማሽመድመዱን ድርጅቱ ገልጿል።