ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 3 ቀናት ወደ አረብ አገር እንወስዳችሁዋለን በሚል የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕ ለማጓጓዝ መሞከሩን ወጣቶች ተናግረዋል።
ወጣቶች እንዳሉት ወደ አረብ አገራት ትሄዳላችሁ ተብለው ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ ወጣቶችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም እያጓጓዙ ሲሆን፣ አንዳንዶች መንገድ ላይ ጠፍተዋል።
ካለፈው አመት ጀምሮ ወታደሮችን ለማሰልጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ የነበረው የኢህአዴግ መንግስት ፣ ከወጣቱ በኩል ያገኘው መልስ ቀዝቃዛ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ የስልጠና ዘዴዎችን እንደሚሰጥ በመግለጽ፣ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለማሰበባሰብ ሲሞክር ቆይቷል።
በሌላ በኩል አርበኞች ግንቦት 7 በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቀ በሁዋላ፣ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት ስልኮችን በመደወል አስተያየቶችን እየላኩ ነው። አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች በዜናው መደሰታቸውንና ትግሉን አጠናክረው እንደሚገፉበት ገልጸዋል