አምስት የህወሃት ሰላዮች ተገደሉ

አምስት የህወሃት ሰላዮች ተገደሉ
(ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በሶማሊላንድ እና አካባቢው በልዩ የስለላ ስራ ሰልጥነው መርጃዎችን ሲያቀብሉ የነበሩ 5 ሰላዮች መገደላቸውን ከደህነነት ምንጮች ለማወቅ ተችሏል::
የሰላዮቹ ጠርናፊ የነበረው አማኑኤል ኪሮስ የተባለው ሰው ድሬደዋ ውስጥ በምስራቅ እዝ አዛዥ ጄኔራል ማሾ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ የተገደለ ሲሆን ፣ 11 ወታደሮችም ለጥየቃ በሚል ተይዘው ታስረዋል::
ግድያውን ማን እንደፈጸመው የታወቀ ነገር የለም ይሁን እንጅ ግድያው የፈጸሙት አውዳል በሚባል ቦታ ላይ ልምምድ የሚሰሩ ታጣቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለ::