ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) እንዳስታወቀው የሰብዓዊ ድጋፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ50 ዓመታት ውስጥ አስከፊ የተባለውን ድርቅ እንዲቋቋም ለማገዝ ነው።
በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሕዝብ ረሃቡን መቋቋም ከሚችለው በላይ እንደሆነበት የገለጸው ተራድኦ ድርጅቱ፣ የዛሬው ተጨማሪ ድጋፍ የሰብዓዊ ምግብ ዕርዳታ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ፣ የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎትና ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድንን ያካተተ ወሳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ያስችላል ብሎአል።
የዲሞክራሲ ፣ የግጭትና የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ተጠባባቂ ረዳት አስተዳዳሪ ቶማስ ኢች ስቶል “ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የአሜሪካ መንግሥት ድርቁ ወደ ብሔራዊ የሰብዓዊ ቀውስ ደረጃ እንዳይሸጋገር “ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
የአሁኑን እርዳታ ጨምሮ የአሜሪካ መንግሥት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2014 ጀምሮ በአጠቃላይ የ705 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የሆላንድ መንግስትም የ 3 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ማድረጉን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።