አሜሪካና አውሮፓ ህብረት በኢህአዴግ ላይ ጠንከር ያለ ዕርምጃ እንዲወስዱ ተጠየቁ

ኢሳት (ጥቅምት 8 ፥ 2009)

የአውሮፓ ህብረት ሆነ የዩናይትድ ስቴስ ኦፍ አሜሪካ በህወሃት/ኢህአዴግ በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንከር ያለ ዕርምጃ እዲወስድው ሂውማን ራይትስ ዎች አሳሰበ።

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው ሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ቀንድ ከፈተኛ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን በተለይ ለኢሳት እንግሊዝኛው ክፍል እንደገለጹት ምዕራብያዊያን ሃገራት ጥቅማቸውን ከማስቀደም ይልቅ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባል።

ፊሊክስ ሆር እንዳሉት በኢትዮጵያ የተከሰተውና የተጠራቀመው የህዝብ ብሶት ለማፈን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ችግሩን ከማባባስ ውጪ መፍትሄ ሊሆን አይችልም ።