ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር ላለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እና ለሶማሊያ መንግስት በመረጃ እና ስለላ ስራ ላይ በመሰማራት ድጋፍ ሰጪ ሆነው ሲያገለግሉ ነበሩ ያላቸውን አምስት ሶማሊያዊያንን አንገት መቅላቱን አልሸባብ አስታውቋል።
አልሸባብ የታይግሎ ከተማን ከተቆጣጠረ ወዲህ በከተማ ያለው ድባብ አስፈሪ ነው። አምስቱን ሰላማዊ ንጹሃን ዜጎችን ጨምሮ ነጋዴዎችና ሌሎች ሰላማዊ ዜጎችም በልሸባብ ሚሊሻዎች በግፍ ተገለው ተጥለዋል ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ እማኝነታቸውን መስጠታቸውን ዠነዋ ዘግቧል።