አለም የፈረንጆችን የ2016 መግቢያ እያከበረ ነው

አውስትራሊያና ኒውዚላንድ 2016 ከሌላው አለም ቀድመው የተቀበሉ ሲሆን፣ በተለይ በአውሮፓ የጸጥታ ቁጥጥሩ በመጥበቁ የበአሉን ድምቀት እንዳይጎዳው ተሰግቷል። የአውሮፓ ህብረት መቀመጫዋ ቤልጂየም፣ በሽብር ስጋት ምክንያት በብራሰልስ ሊታደርግ ያሰበችውን ዝግጅት ሰርዛለች።
የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሸባቸዋለሁ ያለቻቸውን 6 ሰዎች ይዛ አስራለች።
ፈርሳይም እንዲሁ በተለምዶ የምታደርገውን ዝግጅት መሰረዟን አስታውቃለች።
ቱርክ በበአሉ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲዘጋጁ ነበር ያለቻቸውን 2 ሰዎች ይዛ ስታስር፣ ሩስያ በበኩሉዋ ቀዩን አደባባይ መዝጋቱዋን አስታውቃለች።
በበርሊንም እንዲሁ ጥበቃው ተጠናክሮ ቀጥሎአል።