ቻርለስ ቴለር ወደ አፍሪካ ሄደው የእስር ጊዜያቸውን እንዲፈጽሙ ጠየቁ

ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ ቻርለስ ቴለር በሴራሊዮን እኤአ ከ1991-2002 በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸው አለበት በሚል በሄግ ኔዘርላንድስ በተቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት  የ50 አመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

የእስር ጊዜያቸውን በእንግሊዝ የሚያሳልፉት ቴለር፣ 15 ልጆቻቸውን በየጊዜው ለማየት ባለመቻላቸው ወደ ሩዋንዳ ተወስደው እንዲታሰሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

ከቤተሰቦቻቸው እርቀው እንዲታሰሩ መደረጉ አለማቀፍ ህግን የሚጥስ መሆኑን የቴለር ጠበቆች ተናግረዋል። ይሁን እንጅ የእንግሊዝ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተየያት የለም።

ቻልረስ ቴለር በሰሩት ወንጀል የተቀጡ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ናቸው። በስልጣን ላይ ካሉት መሪዎች መካከል የሱዳኑ ጄኔራል አልበሽር በአለማቀፍ ፍርድ ቤት የሚፈለጉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንየታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶም ጉዳያቸው ዘሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት እየታየ ነው።