ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ጁሊየስ ማሌማ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር የተሰኘ ፓርቲ መስርቷል።
ወጣቱ ፖለቲከኛ በነጮች የተያዙት የአገሪቱ መሬት ለህዝቡ እንዲከፋፈል እና ዋና ዋና የማእድን ፋብሪካዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንደሚታገል አስታውቋል።
ማሌማ ፓርቲው ጸረ ካፒታሊዝም መሆኑም ገልጿል።
“እኛ ጥቁሮች በዚህ አገር ስንኖር የምናሳያው ነገር የለንም፣ ልናሳየው የሚገባ ነገር ያስፈልገናል” ብሎአል ማሌማ።
ማሌማ ዘረኛ የፖለቲካ አቋም ያራምዳል በሚል ከአፍሪካ ብሄራዊ ምክር ቤት አባልነት መባረሩ ይታወሳል።