ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሞባይል ስርጭት ተጠቃሚ ወደ 50 ሚሊዮን ለማሳደግ የተደረገ ነው ተብሎአል።
መንግስት ለዘርፉ ከመደበው 1 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ከፊሉን ለሌላው የቻይና ኩባንያ ሀዋይ መስጠቱ ታውቋል።
ሁለቱም የቻይና ኩባንያዎች የመንግስትን የስልክና የሌሎች የመገናኛ መንገዶች ጠለፋ አቅም እንደሚያዳብሩለት ኢሳት ምንጮችን በመግለጽ መዘገቡ ይታወሳል።
የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ዋልታ በሰራው ዜና ለ80 ሚሊዮን ህዝብ አንድ ብቻ የስልክ አገልግሎት የሚጠጥ ኩባንያ መኖሩን እንዲሁም በአፍሪካ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎትን በመንግስት ቁጥጥር ስር ካደረጉ ጥቂት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑን ዘግቧል።