ሚያዝያ ፬ (አራት)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ለኢሳት በላኩት መግለጫ በበለሳ ወረዳ ባጃየ ንኡስ ወረዳ ሚያዚያ 4 ቀን 2009 ዓም ሌሊት ላይ በወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ታጋዮቹ ለግማሽ ሰአት ያክል አካባቢውን መቆጣጠራቸውንና ያለምንም ጉዳት ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል። ጥቃቱን በተመለከተ በገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ ዘመን በመስተዳድሩ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ከተማዋን የተቆጣጠሩት ወታደሮች ፣ 3 የከተማው ነዋሪዎች መታሰራቸው ታውቋል። አቶ አለሙ ይግዛው፣ አምሳሉ ደሳለኝና አማረ ምስጋናው የተባሉት የከተማው ነዋሪዎች ታጋዮቹን መርተው ጥቃቱ እንዲፈጸም አድርገዋል ተብለው መያዛቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።