ታዋቂው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የዲሲፒሊን ክስ ቀረበባቸው

ታኀሳስ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የህሊና እሰረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ከዚህ በፊት ለሎሚ መጽሄት በሰጡት አስተያየት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ የሽብረተኞች መጠቀሚያ ሆኗል በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበውን ዘገባ በመተቸታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ላይ አስተያየት በመስጠታቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦባቸዋል።

አቶ ተማም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንንና  የጸረ ሽብር ህጉን ታዓማኒነት እንዳይኖረው አድርገዋል በሚል መከሰሳቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። ጉዳዩ የዲሲፒሊን ጉዳይ አለመሆኑን አቶ ተማም ተናግረዋል፡