ቤተ እስራኤላዊያን በአዲስ አበባ የረሃብ አድማ አደረጉ
(ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን ወደ እስራኤል ለመግባት በሚጠባበቁበት ወቅት የአገሪቱ መንግስት ድጎማ ለማቋረጥ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ከዛሬ ረቡእ ጀምሮ በአዲስ በአበባ በሚገኙ ቤተመቅደሶች ሴናጎ ውስጥ በመገኘት የርሃብ አድማ አድርገዋል።
ቤተ እስራኤላዊያኑ ከዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት በጉጉት በሚጠብቁበት ሰዓት በጀት ለማቋረጥ መወሰኑ እንዳሳዘናቸው መግለጻቸውን፣ የረሃብ አድመኞቹን ጠቅሶ ኤቢስ ኒውስ ዘግቧል።
ቤተ እስራኤላውያን ላለፉት 10 ዓመታት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንዳሳለፉ ገልጸዋል።