ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም
ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ግዛት ለቆ እንዲወጣ የተወሰነው የአፍሪካ ህበረት የሰላምና የደህንነት ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።
የኢትዮጵያ ፣ የኬንያ ፣ የዩጋንዳ እና የብሩንዲ ጥምር ጦር ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውን አልሸባብን ለመውጋት በእየአቅጣጫው ዘመቻዎችን መክፈታቸው ይታወሳል።
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱዌሊ ሙሀመድ በበለደወይን መገኘታቸውን ቢቢሲ አክሎ ዘግቧል።
የኢትዮጵያን ጦር 5 ሲ የሚሆኑት የጅቡቲ ሀይሎች ይተኩታል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን በጊዜ ለቆ የሚወጣው ከአራት አመት በፊት የደረሰበትን አይነት ሽንፈት በድጋሜ ላለመቀበል በመፈለግ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።