ባንዲራ በመሥራታቸው በላሊበላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ግርማ ቅባቴ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ታኅሣሥ ፲፩ (አሥራ  አንድ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ለ11 አመታት በፖሊስነት ያገለገሉት አቶ ግርማ ፣ ከ1987 ዓም ወዲህ ስራቸውን በመልቀቅ በዲዛይነር ስራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል።

አቶ ግርማ የኢትዮጵያን ባንዲራ በተለያዩ ዲዛይኖች እየሰሩ መሸጣቸውና ወደ ውጪ መላካቸው ወንጀል ሆኖ ተቆጥሮባቸዋል።

ባለፉት ወራት የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የታሰሩት አቶ ግርማ፤ ፍርድ ቤት እስከቀረቡበት እስከዛሬ ማክሰኞ ድረስ “እኔ ነኝ ያሳሰርኳቸው” የሚል አካል መጥፋቱን ከስፍራው ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አቶ ግርማ በሚቀጥለው አርብ በድጋሜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።