ባለፉት ሁለት አመታት በእሳት አደጋ አንድ ቢሊዮን ብር የሚደርስ ንብረት መውደሙ ታወቀ

ኢሳት (ሰኔ 8 ፥ 2008)

በአዲስ አበባ ከተማና ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በሚደርሱ የእሳት አደጋዎች ጥናትን ያካሄዱ አካላት ባለፉት ሁለት አመታት በደረሱ አደጋዎች ወደ አንድ ቢሊዮን ብር የሚደርስ ንብረት መውደሙን ይፋ አድርጓል።

ከአሜሪካ የልማት ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲና በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን በተካሄደው ጥናት የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ወደ 70 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ ወጪ መደረጉ ታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ከተሞች እየደረሰ ያለውን የእሳት ቃጠሎ ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥናቱ ሃሙስ ባቀረበው የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጡን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።