ባለፈው አመት በርካታ የመካላከያ ሰራዊት አባላት መልቀቃቸውን ወታደሮች ገልጹ

መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚ

ድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር  እርሱ በነበረበት የሁመራ እና በአድሜ

አካካቢዎች በሰራዊቱ ላይ ከፍተኛ ግፍ ሲፈጸም ማያቱን ተናግሯል። ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት አለ የሚለው ወታደሩ፣ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው መከፋፈልና የሞራል ድቀት ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል።

ኢሳት ከመከላከያ ሰራዊት የሚለቁ የሰራዊቱን አባላት በተደጋጋሚ እያነጋገረ ማቅረቡ ይታወቃል።