ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞቹን አባረረ

ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ  በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ በእለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ አባይ መላኩ ፊርማ የተጻፈ ነው።

የፋብሪካው ስራስኪያጅ ሰራተኞች መባረራቸውን አምነው ቁጥራቸው ግን 5 ብቻ ብለዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ ሰራተኞቹ የተባረሩት  ምንም እውቅና የሌለው ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ስላደራጁ ነው ብለዋል