ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና በአለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በምግብ ለስራ ታቅፈው የሚረዱ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ታውቋል።
መንግስት ሴፍቲኔት እያለ በሚጠራው መርሀግብር የታቀፉ ኢትዮጵያውያን ምእራባዊያን ለጋሾች እርዳታቸውን ቢያዘገዩ ወይም ቢያቋርጡ ወደ አስቸኳይ ተረጅነት የሚወርዱ ናቸው።
በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው የምግብ እጥረት የተነሳ በሴፍቲኔት የሚታቀፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ታውቋል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት እንዳስመዘገበ ቢገልጽም፣ ከ15 ኢትዮጵያውያን አንዱ ከውጭ በሚሰፈር እርዳታ የሚኖር መሆኑን መረጃዎች አመለክተዋል።