በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ከተሰጠው ብድር ውስጥ 1 ቢሊዮን ብር አልተመለሰም

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና እንደዘገበው ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለተሰማሩ ማህበራት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር ቢሰጥም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው አልተመለሰም ።

ብድርን በማስመለስ በኩል የቅንጅት እጦት ፣ አስቀድሞ የመስሪያ ቤቶችን ያለማዘጋጀትና የገበያ ትስስሮሽን በበቂ ሁኔታ አለመፍጠር መሰረታዊ ጅግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ገንዘብ ተበድረው  ከሃገር የሚጠፉ ፣ በቂ የሆነ ጥናት ባለማድረግ በገቡበት ስራ ከስረው ብድሩን ለመመለስ የሚቸገሩም አሉ።

አበዳሪው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ገንዘቡን ለማስመለስ ጥረት መጀመሩም በዘገባው ተመልክቷል።