(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) አንድ ናይጄሪያዊ በጣሊያን የመጀመሪያው ጥቁር ሴናተር ሆነው ተመረጡ።
ቶኒ ኢዎቢ የተባለው ናይጄሪያዊ በአውሮፓ ምድር የተመረጠ የመጀመሪያ ጥቁር ሴናተርም ሆኗል ሲል አወድሶታል ናይጄሪያን ፖለቲክስ የተባለው ድረገጽ።
ቶኒ ኢዎቢ የኮምፒዩተር ሳይንስ ባለሙያና ኑሯቸውን ላለፉት 39 አመታት ያህል በጣሊያን ማድረጋቸውም ታውቋል።
በማቶ ሳልቫኒ ፓርቲ ውስጥ ዘረኝነት ከምን ግዜውም በላይ እየታየ ነው በተባለበት በዚህ ሰአት መመረጣቸው ብዙዎችን አስገርሟል።
የቶኒ ኢዎቢ በሴናተርነት መመረጥም በአካባቢው ያለውን የፖለቲካ ድባብ ሊቀይረው ይችላል የሚሉ ግምቶችም በመሰንዘር ላይ ናቸው።
ናይጄሪያዊው ቶኒ ኢዎቢ በጣሊያን ታዋቂ ከሆኑና በስደተኞች ጉዳይ ላይ ከሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶች አንዱ መሆናቸውንም ድረ ገጹ በዘገባው አስፍሯል።