በጓቲማላ የፈነዳው እሳተ ጎመራ የ25 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 27/2010)በጓቲማላ የተቀሰቀሰው እሳተ ጎመራ የ25 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።

ከዋና ከተማዋ ስፒዊን ሮድ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተከሰተ የተባለው እሳተ ጎመራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ማቁሰሉ ታውቋል።

ብናኙና ፍንጣሪው በፍጥነት ወደ መኖሪያዎች እየተዛመተ ነው በተባለው በዚህ እሳተ ጎመራ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ጠፍተዋል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

የሃገሪቱ ዋነኛው አየር መንገድም ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ መዘጋቱ ታውቋል።

የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ጂሚ ሞራሌስ በሃገሪቱ ለ3 ቀናት የሃዘን ቀን አውጀዋል።

ፊዩጎ እሳተ ጎመራ በላቲን አሜሪካ ከሚገኙ እሳተ ጎመራዎች አደገኛው እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።