ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በአዘዞ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ። 24ኛው ክፍለ ጦር ማዘዣ አካባቢ በህዝቡና በመከላከያ እየተደረገ ያለው ውጊያ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ተፋፍሞ መቀጠሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። መከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ እየተጠቀመ መሆኑንም ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
መከላከያ ሰራዊቱ በሻለቃ ዶሽቃ ታግዞ ህዝቡ ላይ እየተኮሰ ሲሆን፣ የታጠቀ የጎንደረ አርሶ አደር ከመከካከያ ሰራዊት ጋር የሚያደርገው የተኩስ ልውውጥ የጎንደር ዙሪያን የጦርነት ቀጠና አስመስሏታል።
የ24ኛ ክ/ጦር በቀጥታ በውጊያው ላይ መሳተፉን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሁለቱም ወገን ስለደረሰ ጉዳት የታወቀ ነገር የለም።
በሌላ በኩል የጎንደር ህዝብ በወሰደው እርምጃ ቀበሌ 18 በእሳት መቃጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ቀበሌው የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት እምብርት የሆነ አካባቢ ነው። የተቆጣው የጎንደር ህዝብ ቀበሌውን በእሳት ማቃጠሉ ተብሏል።