ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 15 ሰዎችን ጭኖ ከጎንደር ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪ ጠዳ ከተማ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ 10 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 4 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።
የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ሲኖ ትራክ እየተባለ በሚጠራ የጭነት ተሽከርካሪ ተመትቶ ሳይገለበጥ እንዳልቀረ ወኪላችን ገልጿል።
አብዛኞቹ ሟቾች ነገ የሚከበረውን ወንቅሸት ገብርኤል ለማክበር በመጓዝ ላይ የነበሩ ናቸው።