በጌዲዮ ዞን ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ የንግድ ድርጅቶች ወደሙ

መስከረም ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በዲላ 6 ሰዎች ተገድለዋል። በዲላና በይርጋጨፌም የንግድ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ግጭቱ የብሄር ግጭት መልክ እንዲይዝ ሆን ተብሎ መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።  ከ1997 ዓም ጀምሮ በዚሁ ቦታ የተነሳ ግጭት መነሳቱን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ችግሩ እንዳይፈታ በማድረጉ የአሁኑ ግጭት መቀስቀሱን ገልጸዋል ።